በኢትዮጵያ የሚገኙ ጦማሪያን፡ ጋዜጠኞች እና የሰበአዊ መብት አራማጆች ከግዜ ወደ ግዜ እየተጠናከረ በሄደው የመንግስት የስለላላ መረብ እና የማስፈራሪያ ዘመቻ ኢላማ ሆነዋል:: መንግስት በባለቤትነት በያዘው የቴሌኮም አገልግሎት በመጠቀም የዜጎችን የመናገር እና የግላዊነት ነጻነትን ይተላለፍል:: በሀገር ውስጥ እና በውጪ የሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲ ድረ ገጾችን :የነጻ ሚዲያ አውታሮችን፡ጦማሮችን እና የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን በሀገር ውስጥ እንዳይነበቡ ማገድ የለት ተለት እውነታ ሆኗል::  በተጨማሪም ጋዜጠኞች፡ጦማሪያን እና የሰብአዊ መብት አራማጆች አስተየቶቻቸውን ከመንግስት አላማ ጋር እንዲያጣጥሙ እና ጽሁፎቻቸውን “ቀዝቀዝ” እንዲያደርጉ ማስፈራራት፡ ማጎሳቆል  ወይም ማሰር 
የተለመደ ክስተት ነው:: ስድስቱ የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ሶስቱ ጋዜጠኞች እስርም ይህንን ሁኔታ የሚያረጋግጥ ነው::ከሀገር ውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊ ዜጎች ሳይቀሩ አውሮፓ በሚገኙ ጋማ ኢንተርናሽናል እና ሃኪንግ ቲም ከሚባሉ ድርጅቶች በኢትዮጵያ መንግስት በተገዙ የስለላ ሶፍትዌሮች ይሰለላሉ:: በአጭሩ የኢትዮጵያ የጦማሪያን ማህበረሰብ ለተያዩ ጥቃቶች እጅግ የተጋለጠ የማህበረሰብ ክፍል::የኢትዮጵያ መንግስት ጦማሪያንን ለመሰለል የተለያዩ ዘዴዎችን ይጠቀማል:: እጅግ አደገኛው ግን ዜጎች በየኮምፒተሮቻቸው ላይ ሳያውቁት በድብቅ የሚጫንባቸው ሸረኛ ሶፍትዌሮችን( malwares) በመጠቀም የሚደረግ ስለላ ነው:: እነኚህ ሸረኛ ሶፍትዌሮች በእንግሊዝኛው malwares በመባል የሚታወቁ ናቸው:: ሸረኛ ሶፍትዌሮች ሰዎች ኢንተርኔትን ሲጠቀሙ በኮምፒውተሩ ሰሌዳ ለመተየብ የተጫኗቸውን ቁልፎች በሙሉ መዝግበው ያስቀራሉ፡ የማለፊያ ቃላትን፡ ድምጽን እና ቪዲዮዎችን ይመዘግባሉ አልፎም የይለፍ ቃሎችን ይጠልፋሉ:: በነዚህ  ሸረኛ ሶፍትዌሮች የተበከለ አንድ ሰነድ  ከኢንተርኔት ላይ ከወረደ ወደ ሌሎች ኮምፒውተሮች በቀላሉ ሊዛመት ይችላል:: 

እንዲህ ያለው በኢትዮጵያ መንግስት የተቀነባበረ ስለላ የሚያሰጋቸው ኢትዮጵያዊ ዜጎች የማይክሮሶፍት ፋይሎችን እና ሌሎች ለጽሁፎች የሚያገለግሉ ተመሳሳይ ፈይሎችን ከኢንተኔት ሳያወርዱ እዛው ኢንተርኔት ላይ እንዳለ ለመጠቀም የሚያስችል  የጉግል ዶክመንትን  በመጠቀም በቀላሉ ሊከላከሉት ይችላሉ:: ነገር ግን ይህ ዘዴ በአሜሪካ መንግስት የሚካሄድውን ስለላ ወይም ጉግል በፍርድ ቤት አስገዳጅነት የተጠቃሚዎችን ዳታ ለመንግስታት በማስረከብ የሚካሄድውን ክትትል ወይም ስለላን አይጨምርም:: 

እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ ጎግል በአማርኛ ቋንቋ የሚሰራ የጉግል ሰነድ አገልግሎት አልነበረውም:: ጦማሪያንም ይህንን ዘዴ በመጠቀም  መንግስት ከሚያደርግባቸው ህገ ወጥ ክትትል እራሳቸውን መከላከል

አይችሉም ነበር:: አሁን ግን ጉግል በአማርኛ ቋንቋ የሚሰራ የጉግል ሰነዶች አገልግሎት ሰለጀመረ ይህንን እጅግ ጠቃሚ መሳሪያ በመጠቀም ጦማሪያን እና ሌሎች ለመንግስት ክትትል የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በሸረኛ ሶፍትዌሮች በሚደረግ ህገ ወጥ ክትትል እና የማለፊያ ቃላት ጠለፋ እራሳቸውን መከላከል ይችላሉ:: የሚከተሉትን ትእዛዛት በመከተል  የጉግል ሰነድ አገልግሎትን በኮምፒተርዎ ላይ ማስጀመር ይቻላል:: 

የአማርኛ ቋንቋ አገልግሎትን በጉግል ድራይቭ ውስጥ ማስጀመሪያ ቅደም ተከተላዊ መመሪያዎች

(ሰነዶች ስንል ከጂሜል ጋር ተመሳሳይ የሆኑትን ማለታችን ነው)

በጉግል ድራይቭ ውስጥ ቋንቋን መቀያየር እጅግ በጣም ቀላል ነው:: በስተቀኝ በኩል ከፍ ብሎ የሚገኝው የማርሽ ምልክት ላይ ጠቅ በማድረግ: ካዛ ቅንብሮችን መምረጥ በመቀጠል  አጠቃላይ በሚለው ስር ቋንቋ ከሚለው ጎን የሚገኝውን ተቆልቋይ ምናሌን ጠቅ ማድረግ ካዛ አማርኛ የሚለው እስኪታይ ድረስ ሸብለል እያደረጉ ወደ ታች መውረድ::

1. የማርሽ መግብር 

2. Language settings:   

የቋንቋ ቅንብሮች 

በጉግል ድራይቭ ውስጥ አንዴ ቋንቋ  ከተቀየረ በኋላ ሰነዶች፡ ሉኮች፡ ስላይዶች እና ስእሎች በተመረጠው ቋንቋ መገኝት ይችላሉ:: ይሄ የእገዛ ጽሁፍ ተጠቃሚዎች እንዴት አድረገው የድራይቭን  የሉኮችን፡ የስላይዶችን እና የስእሎችን ቅንብር ወደሚፈልጉት ቋንቋ መቀየር እንደሚያስችላቸው ቅደም ተከተላዊ መመሪያዎች ያስረዳል::.

ሌሎች የጉግል ምርቶችን እና አገልግሎቶችን በአማርኛ ቋንቋ ለማግኝት የሚያስችሉ መመሪያዎች

ተጠቃሚዎች የጉግልን ምርቶች እና አገልግሎቶችን በሚፈልጉት ቋንቋ ለማግኝት በመለያ ቅንብሮች ስር  የሚገኝውን ቋንቋ የሚለውን https://www.google.com/settings/language. በመጫን መቀየር ይችላሉ:: በተጨማሪም የአማርኛ ቋንቋ ተጠቃሚዎች የአማርኛ ፊደላትን በቀጥታ ማስገባት የሚያስችል ገባሬ የቁልፍ ሰሌዳ እንኳ ባይኖር በአስመሳይ የቁልፍ ሰሌዳ ማስገባት  ይቻላል:: ይህ ገጽታ በጂሜይል፣ በሰነዶች እና በሌሎች የጉግል ውጤቶች ውስጥ ይገኛል::